ድርጅታችን ምቹ ቤት መልቲ ሚዲያ “አገር የሚገነባው በትውልድ ጥራት ነው፡፡” ብሎ በፅኑ ያምናል፡፡ የትውልድ ጥራት የሚመጣው ደግሞ ከመልካም ቤተሰብ ነው፡፡ ምቹ ቤት መልቲ ሚዲያ የተሻለ ትውልድ ካልመጣ አገራዊ ለውጥ ማየት እንደማይቻል ስለሚያምን አጥብቆ ቤተሰብ ላይ ይሰራል፡፡ የምንሠራውን ሥራ ሁሉ የምንሠራው በኢትዮጵያ ውስጥ በፍቅር፣ በጤንነት፣ በመተሳሰብ፣ በመተጋገዝ፣ በአገር እና በወገን ፍቅር እንዲሁም በሁለንተናዊ እድገት ሙሉ የሆነ ቤተሰብ ተፈጥሮ ማየት ስለምንፈልግ ነው፡፡ ላለፉት አራት አመታት ምቹ ቤት የተለያዩ ለቤተሰብ እና ለማህበረሰብ ጠቀሜታ ያለው ሥራዎችን ሰርቷል፡፡ የምቹ ቤት መልቲ ሚዲያ መስራችም በእናቶችና በህፃናት ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት መስራት ከጀመረች ከአስር ዓመታት በላይ አስቆጥራለች፡፡
ምቹ ቤት መልቲ ሚዲያ በአመቱ ውስጥ ወደ አስር የሚጠጉ ከቤተሰብ ህይዎት ጋር የተያያዙ ኩነቶችን፣ በሳምንት ሁለት ጊዜ በምቹ ቤት ቢሮ የሚካሄዱ የቤተሰብ ውይይቶችን ያካሂዳል፡፡ እንዲሁም በአገሬ ቴሌቪዥን በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ5፡00-6፡00 በያዘው የአየር ሰዓት በአገር መልካም ግንባታ ላይ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት፣ የማሳሰቢያ፣ የማንቂያ እና የማስተማሪያ ፕሮግራሞችን፣ በማዘጋጀትና በማሰራጨት እንቅፋቶችን ለማስወገድ እና የሚታይ ለውጥ ለማምጣት እየተጋ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመሥራት ጠቃሚ አስተሳሰቦችን በማህበረሰባችን ህሊና ለማስረፅ እና በአገራችን የምንፈልገው ለውጥ እንድናይ የሚያግዝ ሥራ ይሰራል፡፡ በ2014 ዓ.ም ከትምህርት ሚኒስቴር በደረሰን ጥያቄ መሠረት ዓለም ዓቀፍ የልጃገረዶች ቀንን ምክንያት በማድረግ 1050 በላይ ለሚሆን ልጃገረዶች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ እንዲሁም ዘ አፍሪካን ፕሮሚስ ኢትዮጵያ አማካኝነት ለሌሎች ልጃገረዶች የንፅህና መጠበቂያ አበርክቷል፡፡
ምቹ ቤት መልቲ ሚዲያ የሚተገብረው እና የጋራ አገራዊ ራዕይ ያለው በመሆኑ ደሰታ ይሰማናል፡፡ ስለሆነም ስፖንሰር ያድርጉን፤ ለአገራችን ያቀዳችሁትን እቅድ አብረን በመስራት እውን እንድናደርገው መልካም ትብብራችሁን እንሻለን፡፡