አስቸኳይ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ለተቃጠለው በባሕርዳር ሰላም አርጊው ማርያም የአብነት ተማሪዎች

cause-image
  • Started by: Esubalew Geletu
  • For: logo.jpg
  • Started on: 07 apr 2022
  • Closing Date: 15 sep 2022

መጋቢት 27 ለ 28 ሌሊት ባልታወቀ ምክንያት በባሕር ዳር የደብረ ጽዮን ሰላም አርጊው ማርያም ቤተ ክርስቲያን አብነት ጉባኤ ቤት ሙሉ በሙሉ በመቃጠሉ እና ከ2000 በላይ ተማሪዎች ካለመጠለያ በመቅረታቸው የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምእመናን ለተማሪዎች እንዲደርሱላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

መነሻው ምክንያት እየተጣራ እንደሆነ የተገለጸው ድንገተኛው የእሳት አደጋ ደቀ መዛሙርት ይኖሩባቸው የነበሩ ከአራት መቶ በላይ ጎጆችና የደቀ መዛሙርት ንብረት ሙሉ ሙሉ መውደሙም ተገልጿል።

የእሳት ቃጠሎው ያደረሰው አደጋ መጠነ ሰፊ ቢሆንም የእግዚአብሔር ጥበቃም የታየበትና ምንም የተጎዳ ተማሪ የለም።

ምእመናን ለተማሪዎች የዕለት መጠለያ እና ምግብ እንዲሁም ለወደፊት በቋሚነት ለመሥራት እርዳታቸውን እንዲያደርጉ በአክብሮት ተጠይቋል።

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 109,665 of ETB 500,000 22%