- Started on: 09 dec 2024
- Closing Date: 28 feb 2025
ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል ላለፉት ዓመታት በጋሞና አካባቢው ዞኖች እና ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ስር የገጠሪቱን ቤተክርስቲያን አገልግሎቶች በማጠናከር ኢ-አማንያንን በማስተማር.ከአንድ መቶ አሥራ ሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑትን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነት እንዲመጡ አድርጓል፡፡
ነገር ግን አሁንም በገጠርና ጠረፋማ ያሉ በርካታ ወገኖቻችን እኛንም አጥምቁን፣ ኦርቶዶክስ አድርጉን፣ ክርስቲያን መሆን እንፈልጋለን እያሉ ዕለት ዕለት እየተማጸኑ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም አንድ ቀን ክርስቲያን እንሆናለን ብለው በተስፋ የሚጠባበቁ ወገኖቻችንን አስተምሮ እና አስጠምቆ ኦርቶዶክስ ለማድረግ ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል ታኅሳስ 6 ቀን 2017ዓ.ም. ኅብረታችን ለቤተክርስቲያን በሚል መሪ ቃል በጋሞ ባሕል አዳራሽ የገቢ ማሰባሰቢያ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቷል፡፡ እርስዎም ባሉበት ሆነው ይህንን ፕሮጀክት እንዲደግፉ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ኑ ! ተባብረን እንድረስላቸው
Copyright 2024 - Wegenfund | Powered by WegenTech