- Started on: 16 mar 2024
- Closing Date: 31 aug 2025
በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ!
የእውነተኛ ደስታ ምንጭ እግዚአብሔር ነው።
እውነተኛ ፀሐየ ጽድቅ ከድንግልማርያም እቅፍ ታይቷል
የእውነተኛ ሰላም መገኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያን ነች።
የነፍስ ምግቧ ከየኔታ ይደገሳል።
የኔታ ወንበር ተክለው ትውልዱን በቃለ እግዚአብሔር በባህል በእሴት እየቀረጹ የዛሬ ተማሪን ለነገ ካህን አድርገው ለነፍሳችን ስርየትን ያሰጣሉ።
ይህ ወንበር ቢፈርስ የኔታም ከቦታቸው ባይገኙ የነፍስ መብል ጠፍቶ መንጋው ተበትኖ በክፉ ተኩላ በተበላ ነበር።
የኔታ የክርስትና ህይወት ፣የበረከት ፍሬ፣ የሀገር ፍቅር ስላላቸው ዘወትር ቃለ እግዚአብሔርን በመናገር የጠመመውን ሲያቀኑ ፣ ቅኔን ሲዘርፉ፣መፅሐፉትን ሲደጉሱ፣ዜና መዋዕላትን ሲደርሱ፣ሌት ተቀን ከማሓሌቱ፣ከሰዐታቱ፣ከጉባኤ ቤቱ ሳይለዮ ደቀ መዝሙር አፍርተዋል።
የኔ ተማሪም ቀዬውን ትቶ ደበሎ ለብሶ በእንተ ስማ ለማርያም በማለት በልጅነት እድሜ ሀገር ለሀገር በመዞር ምሥጢርን ከአባቶቹ ሲማር ከምእመናን ደጃፍ እየተዘከረ ንባቡን ሲቀፅል ቅኔውን ሲዘርፍ ምሥጢርን እያየ ያየውን በቅኔው እያመሰጠረ በቃለ እግዚአብሔር ይመሰጣል ይራቀቃል::
በእንተ ስማ ለማርያም ብሎ ደጅ ጠንቶ ስንቅ አገልግሉ ወላዲተ አምላክን አድርጎ በነገ ተስፋ ዛሬን ይታገላል።
የቀየው ሰው የእማምላክን ስም ስንቁ አድርጎ በስሟ ተማፅኖ ለመጣው ተማሪ በፍጹም ፍቅር እና ቅርበት "የኔ ተማሪ መጣ.." እያሉ ከቤት የተገኘውን ጥሬም ይሁን ብስል እየለገሱ መጋቢ እና ሞግዚት በመሆን የዛሬን ተማሪ የነገን ካህን ያለመሰልቸት ያስትምራሉ።
ዛሬ ላይ ግን አብሮነት መንምኖ ትውልድን ያስተሳሰረው የአብሮነት ሰንሰለት ተበጥሶ ፍቅር ከቤታችን ሆነ ከልባችን በተሰደደበት በእኛ ዘመን ተሜ ቃለ እግዚአብሔርን እንደተራበ ጥበብን እንደናፈቃት ሳያገኛት በምኞት ይቀራል።
ማህበር ቁስቋም አንደኛ አላማው ከሆነው መካከል የቅድስት ሥላሴ ቤተ- መቅደስ የሆነውን የሰው ልጅ በዕውቀት በምግባር ማነጽ ነው። ለዕውቀት ቤቷ የየኔታ ደጅ መሆኑን በማመን በጥናት ባለሙያች ጉዳዩን በማስመልከት በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በማስተቸት የመፍትሄ ሃሳብ በመያዝ ለአብነት ተማሪዎች የምግብ ፣ የመጽሀፍት ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ፣ የህክምና አገልግሎት ፣ መኖሪያ እስከ ማንበቢያ ቤተመጽሐፍት ለማቅረብ የቀደመ ቀናኢነታችሁን በማመን ሥራውን ጀምሯል።
በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ!
የአብነት ትምህርት ቤትን መደገፍ በወጀብ የማይናወፅ በአለት ላይ የተገነባን የዕውቀት መንደር መፍጠር ነው።
ሀገሬ ታሪኳ ሳይጠፋ ቤተክርስቲያኔ ዕሴቷ ሳይጓደል ለልጄ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ እጁን ይዘርጋ።
የባለታሪክ ልጆችነን እና ታሪክ ላይ ጥቂቷን በማድረግ ታሪክ እንስራ ።
ከእውቀት ገጽ የጎደለ ትውልድ እያፈራች ያለች ዓለምን የሚያሸንፈው እምነታችንን በእውቀት የሚከተሉ የነገ ትውልዶችን መደገፍ ለነፍስ ለስጋ በረከት ነው። የዚህ ዓለም ትርጉም በመንፈሳዊነት የሚመዘንበት በጥበብ መነጽር ቤተክርስቲያን የምትታይበት የየኔታን መንደር በመደገፍ ከፍ እናድርጋት።
ከመላው ዓለም ለመደገፍ በወገንፈንድ ይደግፉ።
እንደዚሁም
በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ:-3900
በአቢሲኒያ ባንክ:-6230
በአካል ተግኝቶ ድጋፍ ለመስጠት የካ ፖሊስ መምሪያ እልፍ ጸጋ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የማዕከሉ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት
ለበለጠ መረጃ፦ በነጻ አጭር የስልክ መስመር +2519066 ፣ +251938644444 ወይም +251116586411
በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ!
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech