- Started on: 12 feb 2025
- Closing Date: 28 feb 2025
መቄዶንያ ከ8 ሺ በላይ የሚሆኑ ምንም ጧሪ እና ደጋፊ የሌላቸው አረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማንን ከመላው ኢትዮጵያ በመሰብሰብ በ44 ቅርንጫፎቹ በመጦር አና በመንከባከብ ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት ባለ 12 ፎቅ ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ እየገነባ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ ከ20,000 በላይ አረጋውያንን እና የአእምሮ ህሙማንን መንከባከብ ያስችላል። ሰይፉ ኦን ኢቢኤስ (Seifu on EBS) የ5 ቢሊየን የገቢ ማሰባሰብ ግብ አድርጎ ቅዳሜ የካቲት 1 ቀን (08 Feb 2025) ጀምሮ በሰይፉ ኢቢኤስ ዩቲዩብ ቻነል ላይ በቀጥታ ድጋፍ እያሰባሰበ ይገኛል።
ይህን ሕንጻ ለመጨረስ እና ሌሎች ማስፋፊያዎችን ለመሥራት ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ሁሉ ለጋስነትዎን በወገንፈንድ በኩል እንዲያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው።” ዶ/ር ቢንያም በለጠ
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech