ብቻውን ያለ እናት ልጆቹን የሚያሳድግ አባት ልመና - እባካችሁ ልጄን አድኑልኝ

cause-image
  • Started by: Tigist Getachew Bulto
  • For: The Organiser (Personal)
  • Started on: 05 jun 2023
  • Closing Date: 31 may 2025

ህፃን ብሌን አሸናፊ ትባላለች የስምንት ዓመት ልጅ ስትሆን በአ.አ ከተማ መከኒሳ ቆሬ ልዮ ቦታው 2 እና 5 ቁጥር ባስ ማዞርያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከወላጅ አባቷ ጋር የምትኖር ስትሆን ህፃን ብሌን ከተወለደች ጀምሮ እስካሁን በአልጋ ላይ ያለች እና እንደ እኩዮቿ መቦረቅ እና መጫወት ያልታደለች ፣ መማር በነበረባት እድሜ ከትምህርት ቤት ይልቅ በአልጋዋ ላይ እንድትውል የተገደደች ህፃን ነች ።

ህፃን ብሌን ለ8 ዓመት
* የማታወራ
* የማትቀመጥ
* የማትራመድ
* እራበኝ ጠማኝ የማትል
* እንዲሁም በዳይፕር የምትፀዳዳ ስትሆን

የሚያሳድጋት ወላጅ አባትዋ በመንገድ ፅዳት ስራላይ የተሰማራ እና በአነስተኛ የገቢ ምንጭ (ደሞዝ) የሚተዳደር ሲሆን ልጁን ለማሳከም አቅም የሌለው ነው።

ህፃን ብሌን የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ (Hydrocephales) እንዲሁም በሚያንቀጠቅጣት ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች። ነገር ግን አሁን የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የዶክተሮች ቦርድ አማካኝነት በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሀገር ወጥታ መታከም እንድትችል ወስኖ ማስረጃ እና የህክምናውን አይነት ገልፀው ፅፈውላታል ። በመሆኑም ለህክምናውም የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ሶስት (3)ሚሊየን ብር ወይም 55,000.00 የአሜሪካን ዶላር ነው ።

ውድ የሀገሬ ልጆች, ሀገር ውስጥም በባህር ማዶ ያላችሁ እባካችሁ ልጄን አድኑልኝ እያልኩኝ በፈጣሪ ስም እለምናችዋለው።

አባትዋ አሸናፊ አሰፋ

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 41,484 of ETB 1,000,000 4%