- Started on: 30 mar 2025
- Closing Date: 31 dec 2025
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የአራቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት ደቀመዛሙርትን በሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ፣በብሉይ ኪዳይ ትርጓሜ፣ በመጽሐፈ ሊቃውንት በሊቀ ሊቃውንት ስማዓ ኮነ መለአክ መምህርነት አያስተማረ እና እያስመረቀ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ጉባኤ ቤት ከመደበኛው የጉባኤ ቤት ትምህርት ጎን ለጎን የሕጻናት የሥነ ምግባር እና መንፈሳዊ ዕውቀት ማዕከል የሚሆን ጌሰም የተተኪ ሕፃናት ማስተማርያ የተባለ ከመለዋ ዓለም (ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ) ያሉ ልጆች የሚማሩበት ት/ቤት እየገነባ ይገኛል።
ጌሰም የተተኪ ሕፃናት ማስተማርያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለወደፊቱ ትውልድ እንዲቀጥል ለማድረግ የተመሰረተ ሲሆን፣ ዋናው አላማ በሃይማኖት፣ በሀገራዊ ታሪክ እና በግብረ ገብ ትምህርት የታነጹ ተተኪ ሕፃናትን ማፍራት ነው። ትምህርቱ የግእዝ ቋንቋ፣ የቤተ ክርስቲያን ጸሎቶች፣ የመዓርገ ዲቁና ስልጠና እና የጥበበ ዕድ ክህሎቶችን (ሥነ ሥዕል፣ ጽሕፈት) ያካትታል። በተጨማሪም፣ የወላጆች፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና የዲያስፖራ ተማሪዎች ትብብር የማህበረሰብ ተሳትፎን ያጠናክራል።
የመማርያው መዋቅር የትምህርት ክፍሎች፣ ቤተ መጽሕፍት፣ ኮምፒውተር ክፍል እና የተማሪዎች ማደሪያ ያካትታል። ፕሮጀክቱ በልጆች ላይ የሃይማኖት እና የሀገር ታሪክ እውቀትን ሲያጠናክር፣ በማህበረሰቡ ላይ የጋራ እሴቶችን በማስተማር የቤተሰብ እና የማህበራዊ ውዴታን ያጠናክራል። በዘላቂነት ላይ ደግሞ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተላለፍ ያበረታታል።
ፕሮጀክቱ ጠቅላላ በጀቱ 20,000,000 ብር ሲሆን፣ ይህም ለግንባታ፣ ለትምህርት መሳሪያዎች እና ለሰው ኃይል ይሆናል። በየዓመቱ በትምህርቱ እና በግብረገብነት የበቁ ወንድ ልጆች ለመዓርገ ዲቁና ዝግጁ በማድረግ የዲቁና ማእረግ ያሰጣል። ከ300 ተማሪዎች በዓመት የሃይማኖት እና የታሪክ ትምህርት እየተቀበለ እንዲያጠኑ ያደርጋል። በዚህ ትምህርት ቤት የውጭ ሀገር ተማሪዎች በክረምት ወደ ሀገር ቤት በመምጣት ይማራሉ።
ይህን ፕሮጀከት እውን ለማድረግ ከመላው ዓለም ያአላችሁ ኢትዮጵያውያን በወገንፈንድ በኩል እንድታግዙን በአክብሮት እንጠይቃለን።
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት ጌሠም የተተኪ ሕጻናት ት/ክፍል አስተባባሪ ኮሚቴ
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech