- Started on: 15 feb 2022
- Closing Date: 27 oct 2026
ምክንያት:- የኢትዮጵያ አትሌቶች ምንጮች እንዳይነጥፉ እንትጋ!
«ሥፖርትና ልማት ኢትዮጵያ» በሚል ሥያሜ የተቋቋመው ይህ ሀገር አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት በአጠቃላይ በሥፖርቱ ዘርፍ በተለይም ደግሞ አትሌቲክስ ላይ ትኩረት በማድረግ ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል አንስቶ ያሉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ስፖርትን ለሀገር ልማት እና ዕድገት ለማዋል የሚያስችሉ ስልቶችን መንደፍ እና መሰረተ ልማቶችን ማሟላትን ያለመ ተቋም ነው።
ስፖርት እና ልማት ኢትዮጵያ ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች መካከል፦
- ከኮማንደር ደራርቱ ቱሉ አንስቶ እስከ ገንዘቤ ዲባባ ድረስ በአትሌቶች ማህጸን በሆነችው በቆጂ አያሌ አትሌቶችን ያፈሩ ድንቅ አሰልጣኝ ጎን በመሆን ለመጥፋት የተቃረበውን የበቆጂ አትሌቶች ምንጭነት ወደ ነበረበት መመለስ፤
- ጀማሪ አትሌቶች በገንዘብ እጦት ምክንያት ከልምምድ እንዳይርቁ ለማስቻል መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት፤
- በዓመት ቢያንስ አንድ ግዜ ሩጫ፣ የሳይክል ውድድር እና ተራራ መውጣትን ያካተተ የሥፖርት ሀገርኛ ቱሪዝም (eco-tourism) ማስጀመር እና ማስተባበር፤
- ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቱሪዝም መሰረት መጣል፤
- በተመረጡ የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስቶች እና የከተማ አስተዳደሮች ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ማቋቋም የሚል ይገኝበታል።
Cause – Let's rescue endangered Ethiopian Athletes’ Sources
The Charitable association named <<Sport and Development Ethiopia>> aims at strengthening and promoting Sport in general and athletics in particular by defining strategies and availing requisite sport infrastructure with a focus towards grass-root level.
Among others, SDE shall:-
- Help Ethiopian Athletes source town rejuvenate via working with the famous coach who produced the renowned Ethiopian runners from Commander Derartu Tulu all the way to Genzebe Dibaba from Bekoji;
- Satisfy needs of beginner athletes who are economically challenged with basic necessities so sustain life in towns;
- Conduct Sport Eco-Tourism that includes running, biking, and hiking at least once per annum;
- Lay foundation to Athletics Tourism in Ethiopia;
- Establish Multipurpose Sport Centers in selected regional administration and City Administrations in Ethiopia.
Picture credit: Theatlantic
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech