- Legal Name: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋግኽምራ ሀገረ ስብከት
- Fundraising Since: 25 jan 2022
- Registraition number: 3814
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋግኽምራ ሀገረ ስብከት
በሀገራችን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት እና ጦርነቱ ባስከተላቸው ቀውሶች ምክንያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ኦርቶዶክሳውያንና ሌሎች ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ። ጦርነቱ ከባድ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎች መሃል የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት አንዱ ነው (ሰቆጣ እና አካባቢው)። በዚህ አካባቢ ከአምስት ወር በላይ በተካሄደው ጦርነት ብዙ ዜጎች ሕይወታቸው አልፏል፣ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል፣ ጉባኤ ቤቶች ተፈትተዋል፣ ገዳማውያንና ዜጎች ፈልሰዋል።
በአሁኑ ወቅት አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም የአካባቢው አባወራዎች ከነቤተሰቦቻቸው ከዕለት ጉርስ ጀምሮ ልዩ ልዩ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፣ ከ600 በላይ የሚደርሱ አብያተ ክርስቲያናት መቀደሻ ዕጣን እና ጧፍ የላቸውም፣ አገልጋይ ካህናት እንዲሁም የአብነት መምህራን እና ተማሪዎችም ምግብ እና መሠረታዊ ፍላጎቶች የሚያስፈልግበት ወቅት ነው። ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ለወገናችሁ በምትችሉት ሁሉ በዚህ በወገን ፈንድ በኩል እርዳታችሁን እንድታደርሱልን ጥራያችንን እናስተላልፋለን።
Whatever you choose, thank you!
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech