- Legal Name: Menbere Tsebaot Kidist Selase Catedral
- Fundraising Since: 20 feb 2024
Menbere Tsebaot Kidist Selase Catedral
በቀደሙት አባቶቻችን ጥረት የቆዩልንና አገራችን በዓለም መድረክ በበጎ መልኳ እንድትታወቅ ያደረጉ ቅርሶቻችንን ትላንት በነበሩበት ሁኔታ ልንጠብቃቸውና ልንከባከባቸው ይገባል፡፡ ከነዚህ ቅርሶቻችን መካከል አንዱ የሆነው በከተማችን እምብርት ላይ በአራት ኪሎ ቤተመንግስት አጠገብ የሚገኘው የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነው፡፡ ካቴድራሉ ለቤተክርስቲያናችን ከአክሱም ጽዮን ቀጥሎ ሁለተኛው ታላቅ ሥፍራ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የራሷን ፓትርያርክ መሾም ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የቅዱሳን ፓትርያርኮች እና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሹመት የሚፈጸምበት እንዲሁም በዓለ ሲመት እና ተያያዥ ኩነቶች የሚካሄድበትና የሚከበርበት ብቸኛ ቤተ መቅደስ በመሆኑ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አገራችንን በቤተ መንግስት እና በቤተ ክህነት ደረጃ በከፍተኛ የመሪነት ቦታ ላይ ሆነው ይመሩ የነበሩ እንዲሁም የአገራችን ዳር ድንበሯ ተጠብቆ በነጻነት የምንኖርባት ነጻ አገርን ያስረከቡን በርካታ የሃይማኖት አባቶች፣ አርበኞች ፣ጀግኖች እና የጦር መኮንኖች መካነ እረፍት ሥፍራ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በእውቀታቸው፣ በጥበባቸው ፣ በበጎ አድራጎት ሥራቸው የሚታወቁ ሰዎችም የመካነ መቃብር ሥፍራ በመሆን እያገለገለ ያለ መካን ነው፡፡ ይህን ቅርስ እና ታሪካዊ ሥፍራ መደገፍ እና ወደ ቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኃለፊነት ነው፡፡ ስለሆነም ወገን ፈንድ በሚባለው የገቢ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ በመጠቀም በልዩ ልዩ የአለማችን ክፍሎች የምትገኙ ምእመናን እና ኢትዮጵያዊያን ለመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዕድሳት እግዛ በማድረግ ከበረከቱ እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠራለን።
Whatever you choose, thank you!
Copyright 2024 - Wegenfund | Powered by WegenTech