- Legal Name: Pagumen amst (5) charity organization
- Fundraising Since: 01 sep 2023
- Registraition number: 4431
- Email: peagumeamst88@gmail…
- Website: pagumenamstcharity.…
Pagumen amst (5) charity organization
ጳጉሜን አምስት (፭) ግብረሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ህጎች መሰረት የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱም ጳጉሜን አምስት ቀን 2011 ዓ/ም ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በመዝገብ ቁጥር 4434 ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነትን አግኝቷል፡፡ ድርጅቱ በዋናነት አላማውን ጎዳና ላይ ያሉ ችግረኛ እና ምስኪን ወገኖቻችን ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት የሚችል ጉልበት፤መማር የሚችል አእምሮ ይዘው በማምረቻ ዘመናቸው በተለዩ ምክንያት ወደጎዳና በመውጣት ለተለያዩ አደንዛዥ ዕፅ እና ሱስ ተጋልጠው ለመንግስትም ሆነ ለህብረተሰቡ ትልቅ ተግዳሮት የሆኑትን ከጎዳና ላይ በማንሳት እራሳቸውን እስኪችሉ አስፈላጊ የሚባለውን ስልጠና እና ድጋፍ በመስት ከተረጂነት ወደረጂነት እያሸጋገረ የሚገኝ ግብረሰናይ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅቱም በዋናነት ከጎዳና ላይ አንስቶ ቤት ተከራይቶ በማኖር
• የስነልቦና ስልጠና በመስጠት
• እራሳቸውን እስኪችሉ አስፈላጊውን ወጪ በመሸፈን
• ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ
• ስራ እንዲሰሩ በማድረግ
• የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በማመቻቸት
• የአልባሳት እና ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ
• ከመጡበት ወደቤተሰቦቻቸው መመለስ የሚፈልጉትን ወጫቸውን በመሸፈን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በማስታረቅ ሽኝት ማድረግ እና ባሉበት ሆነው ስራ እየሰሩ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲረዱ በማድረግ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ተቋርጦ የነበረውን የቤተሰብ ግንኙነት በመመለስ ቤተሰባዊ ትስስር እንዲቀጥል በማድረግ ከተረጂነት ወደረጂነት እያሸጋገረ ይገኛል፡፡
ይህ አገር በቀል ድርጅት ወደፊትም ይህንኑ ስራውን ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠል ጎደና ላይ ያሉ መሰል ችግረኛ እና ምስኪን ወገኖቻችንን ከጎዳና ለማንሳት አቅዷል፡፡ ይህንን አገልግሎትም በመላው ሃገሪቱ እንዲስፋፋ እና ሁሉም ማህበረሰብ እርስ በእር በመረዳዳት ወይም እጅ ለእጅ በመየያዝ እና በመደጋገፍ የራሳችንን ችግር እራሳችን እንድንፈታ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ይህንን የተቀደሰ አላማ አብሮን መስራት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆን ድርጅት ወይም ተቋም በራችን ክፍት ነው፡፡ አብረን ተባብረን በመስራት ለሀገራችን እና ለወገኖቻችን አለኝታ እንሁናቸው በማለት የነፍስም የስጋም ዋጋ የሚያገኙበትን ጥሪ ስናቀርብልዎ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡
Whatever you choose, thank you!
Copyright 2024 - Wegenfund | Powered by WegenTech