- Legal Name: ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም
- Fundraising Since: 17 dec 2023
- Phone: +251911639820
- Email: ramagedam16@gmail.c…
- Website: ramakidanemheretged…
ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም
ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም ከዛሬ 1300 ዓመታት በፊት በጊዜው ከባይዛንታይን ግዛት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ዘጠኙ ቅዱሳን መካከል በአባ ገሪማ እና በአባ ጉባ አማካይነት የተመሠረተች ጥንታዊት ገዳም ናት። ገዳሟ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ወረዳ ዞብል አካባቢ የምትገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ 567 ኪሎ ሜትር ትርቃለች።
ገዳሟ በተከታታይ የዝናብ እጥረት ያለበት አካባቢ ላይ የምትገኝ በመሆኗ በቂ ምርት የማይመረት ከመሆኑም በላይ የሚዘራውም እህል ፍሬ ሳያፈራ ባለበት ይቀራል። በዚህም ምክንያት አካባቢው ለድርቅ የተጋለጠ እና ኑሮውም አመርቂ አይደለም። በራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳም ውስጥ 24 ሰዓት ያለማቋረጥ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ 300 ያህል መናንያን እና ከ200 ያላነሱ የአብነት ተማሪዎች ይገኛሉ።
ባለፉት 4 ዓመታት በኮቪድ ወረርሽኝ፣ በአካባቢው ባለው የተራዘመ ጦርነት ምክንያት የገዳሟ ወዳጆች ወደዚህች የተቀደሰች ሥፍራ መጓዝ አልቻሉም። ይህም ያለውን ችግር በይበልጥ አባብሶታል። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ይህንን በመገንዘብ ለገዳሟ መናንያን እና የአብነት ተማሪዎች ቀለብ የሚሆኑ እህሎችን ለምሳሌ ዳጉሳ፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ በርበሬ እና የመሳሰሉትን ገዝቶ በማቅረብ ወይም በገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉ ገዳሟ ጥሪ ታደርጋለች። የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ፣ በገዳሟ አካውንት ቁጥር፦ አቢሲኒያ ባንክ፤ አካውንት ቁጥር 6973426
በበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥሮች ፦ +251911639820/+251911333632/+251920052423 ይደውሉ።
Whatever you choose, thank you!
Copyright 2025 - Wegenfund | Powered by WegenTech