የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መንፈሳዊ ፊልም

project-image
  • Started by: Theophoros Pictures PLC
  • For: IMG_20240603_120318_426.png
  • Started on: 13 jun 2024
  • Closing Date: 31 dec 2024
  • YouTube: Play Video

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በ14ኛው መ/ክ/ዘ የተነሱ በርካታ መጻሕፍትን በማዘጋጀት ፣ በዘመናቸውም ሆነ ከዘመናቸውም በፊት ለተነሱ መናፍቃን ምላሽ በመስጠት እና በበርካታ ስራዎች ቤተ ክርስቲያንን ያስጌጡ በአሁኑ ወቅት በሰፊው አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን አርጋኖን ፣ መጽሐፈ ሰአታት ፣ መጽሐፈ ምስጢር እና ሌሎችንም ድርሰቶች ያዘጋጁ አባት ናቸው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ፊልሞችን ማዘጋጀት የተለመደ ባይሆንም እንደ ግብጽ እና ሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት በቀጣይ በርካታ መንፈሳዊ ፊልሞችን ለመስራት መነሻ ሊሆን በሚችል መንገድ ይህን ፊልም መስራት እንዲቻል ከገዳማቸው ጋር ስምምነት ተፈጽሞ ፣ በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ዕውቅና ተሰጥቶት ፣ የስክሪፕቱ መነሻ ጽሑፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ ቅድመ ዝግጅቱ ተጀምሯል። በቀጣይ የሚያስፈልገው ገንዘብ ሲሟላ አንጋፋ የፊልም ባለሙያዎችን አካቶ በብጹዓን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት እና መምህራን ክትትል የፊልሙ ስራ ተከናውኖ በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያም ውጪ በልዩ ኦርቶዶክሳዊ ሲኒማ ባህልን ፈጥሮ ለዕይታ የሚቀርብ ይሆናል።

በመሆኑም ውድ ኦርቶዶክሳውያን ይህን ታላቅ ፊልም ለመስራት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማሟላት ይቻል ዘንድ በተለያየ አማራጭ የቀረቡ ቅድመ ቲኬቶችን በወገንፈንድ በኩል በመግዛት ከበረከቱ ተሳታፊ መሆንና የዚህ ታሪክ አካል መሆን ይችላሉ።
የቅድመ ትኬቶች መጠን
10,000 ብር (200$)
5,000 ብር (100$)
500 ብር (10$)

የሚፈልጉትን መጠን በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ መግዛት ይችላሉ።

የቅዱሳንን ዜና እንናገር ዘንድ ፍቅር ግድ ይለናል።

በተለያዩ አማራጮች የቀረቡ ቅድመ ቲኬቶች በመግዛት የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መንፈሳዊ ፊልምን ስራ ይደግፉ::

Collections so far

(Rounded figure - does NOT affect actual money deposited)

ETB 710 of ETB 5,000,000 0%